ድሬዳዋ —
በወሰኖችና በማንነት ዙሪያ በ68 ዞኖች ላይ ባካሄደው የመጀመሪያ ጥናት ውጤት ላይ ከኅብረትሰቡ ጋር በዝግ ምክክር ማካሄድ መጀመሩን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አስታውቋል።
ድሬ ዳዋ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ህዝባዊ ውይይት ወደፊትም መገናኛ ብዙኃንን እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተ ውይይት እንደሚያካሂድ ኮሚሽኑ ጠቁሞ በአስተዳደር ወሰንና በማንነት ጉዳይ ላይ ያሉ ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል የሚለውን ሃሳብ እንደሚያቀርብ አመልክቷል።