ዋሺንግተን ዲሲ —
የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት መስከረም 21 ቀን የሚውለውን ዓመታዊውን ባህላዊ የእሬቻ በዓል ለማክበር እየተዘጋጁ ባሉበት ባሁኑ ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎቹን እንዲያቅብ
“ሂዩማን ራይትስድ ዋች”
የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ትላንት ይፋ ባደረገው መግለጫው አሳሰቧል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በመጪው የእሬቻ በዓል ላይ የፀጥታ ኃይሎቹን በበለጠ ትዕግስትና ብቃት ለማዘጋጀትና ሁከት እንዳይከሰት ለመከላከል አስችኳይ ዕርምጃዎች እንዲወስድ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚሠራው ድርጅት ጥሪ አስተላልፏል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ