በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ዘግናኝ የመብት ጥሰት በኦጋዴን እስር ቤት"- ሂዩማን ራይትስ ወች


ሂዩማን ራይትስ ወች በሶማሌ ክልል "ኦጋዴን" በተባለው እስር ቤት ውስጥ ይፈፀማል ያለውን የመብት ጥሰት ለማሳየት ያዘጋጀው ስዕል።
ሂዩማን ራይትስ ወች በሶማሌ ክልል "ኦጋዴን" በተባለው እስር ቤት ውስጥ ይፈፀማል ያለውን የመብት ጥሰት ለማሳየት ያዘጋጀው ስዕል።

በሶማሌ ክልል “ኦጋዴን” በተባለው እስር ቤት ሰዎች በዘፈቀደ እየታሰሩ እጅግ አሰቃቂ ተግባር ይፈፀመብቻዋል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ወች ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።በዚህ በማይቋረጥ የመብት ጥሰት ውስጥ የመንግሥት ባላሥልጣናት እጃቸው አለበት ብሏል። የሶማሌ ክልል መንግሥት ሪፖርቱ ከእውነት የራቀ ነው ሲል ማስተባበያ ሰጥቷል።

"ዘግናኝ የመብት ጥሰት በኦጋዴን እስር ቤት"- ሂዩማን ራይትስ ወች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:21 0:00

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ወች “ልክ እንደ ሞቱት ነን” በሚል ርዕስ ዛሬ ባወጣው ባለ 88 ገጽ ሪፖርት ፤ በሶማሌ ክልል ኦጋዴን እስር ቤት በሚል በሚታወቀው እስር ውስጥ ዜጎች በዘፈቀደ ለዓመታት ታስረው አሰቃቂ ስቃይ እና ድብደባ ተፈጽሞውባቸዋል ብሏል።

ሪፖርቱ አያይዞ፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት በኦጋዴን እስር ቤት የሚፈጸም ማሰቃየት እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዘግናኝ እና ያልተቋረጠ ሰቆቃ፣ ድብደባ፣ ማዋረድ፣ በቂ ያልሆነ የሕክምና አገልግሎት፣ በቂ ያልሆነ የቤተሰብ እና የጠበቃ ጉብኝት ይባስ ብሎም አንዳንዴ በቂ ምግብ አለማግኘት በእስር ቤት መፈጸሙን ያትታል። ይህንን ሰቆቃም በመብት ጥሰት የታወቁት የሶማሌ ልዩ ፖሊስ እና የማረሚያ ቤቱ የጸጥታ ሀይሎች ፈፅመውታል ብሏል በሪፖርቱ።

ድርጅቱ ይህንን ሪፖርት ለማዘጋጀት የተለያዩ መረጃዎችን በግብዓት መጠቀሙን ጠቅሶ ፤የመንግስት የጸጥታ ኃይሎችን፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባላሥልጣናትንና 70 የቀድሞ እስረኞችን ጨመሮ በአጠቃላይ ለ100 ሰዎች ቃለ መጠይቅ ማድረጉን አስታውቋል።

ድርጅቱ ቃለ መጠይቅ ያደረገላቸውና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው የተቀየረ የቀድሞ እስረኞች ጠቅሶ በሪፖርቱ ላይ እንዳሰፈረው፤ እስረኞቹን በመላው እስረኞች ፊት ልብሳቸዉን አስወልቀው እርቃናቸውን አድረገው እንደ ደበደቧቸው ያስረዳል።

የሂዩማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፌሊክስ ሆርን ድርጅታቸው ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ ከአሜሪካ ድምፅ ተጠቀው፤ የሶማሌ ክልል እስረኞችን ፍርድቤት ባለማቅረብ በሀገሪቱ ካሉት ከሌሎች እስር ቤቶች የተለየ ነው ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር አቶ ኢድሪስ እስማኤል ከቪኦኤ የሶማሌኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል ተጠይቀው። “ድርጊቱ በክልሉ አልተፈፀመም” ሲሉ አስተባብለዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG