ድሬዳዋ —
በፕሬዚዳንቱ የአስቸኳይ ጊዜ የኤድስ እርዳታ ፔፕፋር አማካኝነት ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እየተደረገ ያለው ድጋፍ የኤችአይቪን ሥርጭት ለመቀነስ ያገዘ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
በተለይ ለኅብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት በአብዛኛው እየተካሄደ ያለው በዚሁ ድጋፍ አማካኝነት መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል ኤችአይቪን ለመዋጋት በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ከሚደረገው ድጋፍ ማሳያዎች አንዱ መሆኑ ተገልጿ፡፡