ድሬዳዋ —
የሐረር ከተማ የውኃ ችግር በከፊል እየተቃለለ መሆኑ እየተሰማ ነው።
ከከተማዪ የውኃ ምንጮች አንዱ የሆነው የኤረር ግድብ አቅርቦት በአካባቢው ነዋሪዎች ተቋርጦ መቆየቱ ተዘግቧል።
ነዋሪዎቹ የአካባቢው የከርሠ-ምድር ውኃ እየተመናመነ ስለሆነ ለእርሻ የሚሆን ውኃ እንዲለቀቅላቸው፣ እንዲሁም ለግድቡና ለውኃ ጣቢያው መሥሪያ ቦታ ሲባል ከይዞታዎቻቸው እንዲነሱ የተደረጉ ሰዎች ቀደም ሲል የተከፈላቸው ካሣ እንዲሻሻልላቸው መጠየቃቸው ተገልጿል።
ክልሉ በነዋሪዎቹ ጥያቄዎች ተስማምቶ ውኃው መለቀቅ መጀመሩን የክልሉ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወለዳ አብዶሽ አመልክተዋል፡፡
ከነዋሪዎቹ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ለመፍትኄው ዘላቂነት አስፈላጊ መሆኑን የክልሉ የፍትህና የፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ዩሱፍ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ