በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከአትሌቲክሱ ዓለም ሊሰናበት ነዉ

በተለያዩ ርቀቶች 27 የዓለም ክብረ ወሰኖችን የሠበረውና በቅርቡም የምንጊዜውም የዓለም ምርጥ አትሌት ተብሎ የተመረጠው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከነገ በስቲያ እሁድ በይፋ ከአትሌቲክሱ ዓለም ይሰናበታል።

በተለያዩ ርቀቶች 27 የዓለም ክብረ ወሰኖችን የሠበረውና በቅርቡም የምንጊዜውም የዓለም ምርጥ አትሌት ተብሎ የተመረጠው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከነገ በስቲያ እሁድ በይፋ ከአትሌቲክሱ ዓለም ይሰናበታል።

ኃይሌ ጡረታ ስለመዉጣት ሃሳቡ ባለፈዉ ግንቦት ወር ማንቸስተር ኢንግላድ ዉስጥ በተደረገዉ ዉድድር ላይ ባለፈዉ ግንቦት ወር የገለጠ ቢሆንም የመጨረሻ ኦፊሴላዊ ስንብቱን በአገሩ ላይ እንደሚያደርግ ገልጿል። ስለዚህም ስንብቱን የሚያደርገዉ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት በራሱ በኃይሌ ገብረ ሥላሴ በተጀመረዉና የፊታችን እሁድ አዲስ አበባ ላይ የሚካሄደዉን ”ታላቁ ሩጫ” በመሳተፍ እንደሚሆን ታውቋል።

እስክንድር ፍሬው የላከዉን ሙሉ ዘገባ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከአትሌቲክሱ ዓለም ሊሰናበት ነዉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:08 0:00

XS
SM
MD
LG