በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃያ ሁለት የሲቪክ ድርጅቶች መግለጫና ጥያቄ፤ የኤርትራ መንግሥት መልዕክት


ሃጫሉ ሁንዴሳ
ሃጫሉ ሁንዴሳ

በሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈት ኀዘናቸውን የገለፁ አሜሪካና ከአሜሪካ ውጭ የሚገኙ ሃያ ሁለት ማኅበረሰባዊ ድርጅቶች አድራጎቱን የፈፀሙ በሕግ እንዲጠየቁ፣ የኮቪድ-19 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲጠናከር፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና ኢትዮጵያዊያን ከመንግሥት ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

ሺካጎ፣ ታላቁ ሲንሲናቲ፣ ቤይ ኤርያ፣ ናሽቪል፣ ላስ ቬጋስ፣ መካከለኛው ኢንዲያና የሚገኙ የኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰቦች፤ የኅዳሴ ግድብ ድጋፍ ስብስቦች በሎስ አንጀለስ፣ በአሪዞና፣ በኦሬገንና በደቡብ ምዕራብ ዋሺንግተን ስቴት፤ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች ማኅበር በደቡብ አፍሪካ፣ ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት፣ ወይም ግሎባል አላያንስ፣ ፎረም 65፣ የኢትዮጵያዊያን ምሁራን ኔትወርክ እና ቪዥን ኢትዮጵያ ወይም ራዕይ ለኢትዮጵያ ባወጡት መግለጫቸው “ዝነኛው ድምጻዊ ወገናችን አቶ ሃጫሉ ሁንዴሳ ትላንት ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥይት የመገደሉን ዜና የሰማነው በታላቅ ሃዘንና ቁጭት ነው። የተሰማንንም ጥልቅ ሃዘን ለባለቤቱ፣ ለልጆቹ፣ ለመላው ቤተሰብና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንገልጻለን።” ብለዋል።

መግለጫው አክሎም “አገራችን ከባድ ፈተናዎች በተጋረጡባትና የልጆቿን የጠነከረ አንድነት በምትሻበት በዚህ ወቅት የተፈጸመ ይህ የወንጀል ድርጊት በወጣቱ ድምጻዊ ወገናችን ላይ ብቻ የተቃጣ ሣይሆን በአገራችን አንድነት፣ በሕዝባችን ሰላምና በአብሮነታችን ላይ የተሰነዘረ ጥቃት አድርገን እንቆጥረዋለን” ብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ ‘የኤርትራ መንግሥት መልዕክት ነው የተባለና የሃገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሠፈሩት መልዕክት “አነቃቂና የፍትህ ታጋይ የሆነው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህይወት በሚያሳዝን ሁኔታ ተቀጭቷል” ይላል።

ለቤተሰቡ፣ ለሚሊዮኖች አድናቂዎቹና ደጋፊዎቹ፣ ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ ህዝብም ልባዊ ኀዘናቸንን እንገልፃለን” ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሃያ ሁለት የሲቪክ ድርጅቶች መግለጫና ጥያቄ፤ የኤርትራ መንግሥት መልዕክት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:19 0:00


XS
SM
MD
LG