በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኃብተሥላሴ ታፈሰ አረፉ


ኃብተሥላሴ ታፈሰ
ኃብተሥላሴ ታፈሰ

ለኢትዮጵያ ቱሪዝም የመሠረት ድንጋይ ያኖሩት ልጅ ኃብተሥላሴ ታፈሰ በ91 ዓመት ዕድሜያቸው ዛሬ ነሐሴ 3/2009 ዓ.ም. አርፈዋል፡፡ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም "ወዳጄ" ሲሉ ያስታውሷቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስና ታሪክ ውርሶች፣ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት - ዩኔስኮ ሰፊ ዕውቅና እንዲያገኝ መሠረት ያኖረ ተግባር የፈፀሙት ሀብተሥላሴ ታፈሰ የጢስ ዓባይ-ጣና-ጎንደር-ላሊበላ-አኵስም የጉብኝት መሥመር እንዲዘረጋና እንዲታወቅ ያደራጁ “የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት” ተብለው የሚታወቁ ናቸው፡፡

ባለብዙ ሙያና ባለብዙ አንደበቱ ልጅ ሀብተሥላሴ ታፈሰ ከቱሪዝም ተግባራቸው ሌላ፣ የልዑል መኮንን ኃይለሥላሴ መታሰቢያ የሆነው፣ የዛሬው ጥቁር አንበሣ ሆስፒታል እንዲታነፅ ለንጉሡ ሃሣብ አቅርበውና አሳምነው ወደ ተግባር እንዲገባም ያደረጉ ሰው ናቸው፡፡

ልጅ ሀብተሥላሴ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬስ ኃላፊ ሆነው ሥራ ከመጀመራቸው በፊት፣ በዩናይትድ ቴትስ በመንግሥት ግንኙነት ጉዳዮች የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት በተፈሪ መኮንን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡

ልጅ ኃብተሥላሴ ወጣት ባለሙያ ሆነው ሥራና መገናኛ ሚኒስቴር ለመቀጠር ባመለከቱ ጊዜ ያኔ የመሥሪያ ቤቱ ሚኒስትር የነበሩት ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም አሁን “ወዳጄ” ብለው ነው የሚያስታውሷቸው። ስለ ትጋታቸውና ታታሪነታቸው፣ ስለመልካም ሰብዕናቸው ለቪኦኤ ተናግረዋል ልዑል ራስ መንገሻ።

ልጅ ኃብተሥላሴ ታፈሰ ሦስት ልጆችን አፍርተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኃብተሥላሴ ታፈሰ አረፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:50 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG