በዛሬው ዕለት በአምቦ ከተማ በሃጫሉ ወላጆች ቤት በተገኙ ማንነታቸው ባልታወቁአስክሬኑን መውሰድ በሚፈልጉ ሰዎችና አስክሬኑ አይወሰድም ባሉ የሃጫሉ አጎትንጨምሮ ሌሎች ቤተሰቦች መካከል ክርክር እንደነበርና በመጨረሻው ወደ ግጭትአምርቶ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ከስፍራው አጠናቅሯል።የሃጫሉ አባትና አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ የልጃቸው በማን ፍላጎት አምቦ እንደሚቀበርተጠይቀው። “በራሳችን ፍላጎት ነው” ብለዋል።
“በቤተሰብ ፈቃድ ነው እዚህ የመጣው። እንደውም ከልክለው ነበር። መንገድ ከደረሰበኋላ መልሰው ወሰዱት። እንደገና ጅማ በር መከላከያ ወሰዱት። እንግዲህ ወሬ ወሬነው የምሰማው እኔ። ከዛ ከጅማ በር ወደ መከላከያ ወስደው ከዚያ በሂሊኮፕተር ወደሆሚቾ ውስደው በአምቡላንስ እንዲመጣ ተደረገ። መንግደ ወጥቼ አክሬንኑንተቀብዬ ወደ ቤት አስገባሁ” ብለዋል።
በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ባልቻ፤“የድምፃዊ ሃጫሉ ሞት ሃገርን በከባድ ልብ ሰባሪ ሐዘን ውስጥ አስገብቷታል” ብለዋል። አያይዘውም፤ “ብሔርን ከብሔር እና ኃይማኖትን ከኃይማኖት ጋራ በማጋጨትሃገር ወደ ብጥብጥ እንድትገባ ግድያውን ከመምራትና እና ከግድያው በኋላ ደግሞአስክሬኑን በማንገላታት አገር ለመረበሽ ያሴሩ የተቀናጁ ሰዎች እጅ አለበት” ብሎመንግሥት እንደሚያምን ገልፀዋል።
እስካሁን መንግሥት ባገኘው መረጃም 50 ንፁሃን ዜጎች በተለያየ መንገድመገደላቸውን ፣ ንብረት መውደሙን እና አካል መጉደሉንም ተናግረዋል። ይህ ዘገባበሚጠናቀርበት ጊዜ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ገልፀው የነበረ ሲሆን ማምሻውንመግለጫ የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራ አራርሳ መርዳሳየተገደሉት ሰዎች 81 መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።
“መንግስት ከዚህ በኋላ ሃገር ሲበጠበጥና ንፁሃን ሲገደሉ ዝም ብሎ አያይም” ያሉትአቶ ጌታቸው፤ የሃጫሉ ሞት የመላው አገሪቱ ሐዘን በመሆኑ ስንብቱ በሰላማዊ መንገድእንዲደረግ ጠይቀዋል።
ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የተወለደው አምቦ ከተማ ሲሆን። በ17 ዓመት ዕድሜው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ማለት ነው በ1995 ዓ.ም አምቦ ከተማ በተማሪዎች እንቅስቃሴ እርሱና ጓደኞቹ የሰው ሕይወት አጥፍታችኋል በሚል ተከሰው ታስረው እንደነበር በቃለ ምልልሶቹ ላይ ቀደም ሲል ተናግሯል።
በመጨረሻም ፍርድ ቤት በነፃ ከአምስት አመት በኋላ በነፃ ያሰናበተው ሲሆን በእስር ላይ እያለ መጻፍ የጀመረውን ሙዚቃ መሥራት ቀጠለ። ነጠላ ዜማ ለመሥራት ጀምሮት የነበረውን የሙዚቃ ሥራ ወደ አልበም በመቀየር “ሳኚ ሞቲ” የተሰኘውን የመጀመሪያውን አልበም ማውጣቱን ወዳጆቹ ይናገራሉ።
ሃጫሉ ወደ ተለያዩ ሃገሮች በመሄድ በኦሮመኛ ቋንቋ ተወዳጅ የሆኑ ሥራዎቹ አቅርቧል። በሞያው እንዲያድግና አልበሙን ከመግዛት ጀምሮ በሙዚቃ ሥራዎቹ ላይ በመታደም እገዛ ያደረጉለት በውጭ የሚገኙ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላትን ደጋግሞ ሲያመሰግን ተሰምቷል። እዚህ ዩናይትድ ስቴትስም አራት ጊዜ መጥቶ በተለያዩ ግዛቶች ተዟዙሮ የሙዚቃ ሥራዎቹን አቅርቧል። “ዋኤ ኬኛ” የተሰኘ ሁለተኛ አልበም እና የተለያዩ ነጠላ ዜማዎችንም ሠርቷል። ሃጫሉ የእርሱ ዘፈኖች የኦሮሞ ሕዝብ መብትን የሚጠይቁ መሆናቸውን ባገኘው መድረክ ላይ ሁሉም ይህንን ሐሳብ የሚያፀባርቅ ሥራን እንደሚሠራ ይናገር ነበር።
ከአባቱ አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ እና ከእናቱ ወ/ሮ ጉደቱ ቦራ የተወለደው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከባለቤቱ ወ/ሮ ፋንቱ ደምሰው ጋር ተጋብቶ አንድ የአምስት፣ የሁለት ዓመትና የአንድ ወር ሦስት ልጆችን ወልዷል።
(አድማጮች የዚህ ዘገባ ዝርዝር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ይጠብቁ)