በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጊኒ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደውን ዲምክራስያዊ የሆነ የፕረዚዳንታዊ ምርጫ


ጊኒ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደውን ዲምክራስያዊ የሆነ የፕረዚዳንታዊ ምርጫ ባለፈው እሁድ አካሂዳለች። ይሁንና በርካት የሀገሪቱ ተወላጆና አለም አቀፍ ታዛቢዎች ስለጊኒ የምርጫ አካሄድ ገና ብዙ መሰራት አለበት ይላሉ።

የጊኒ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው ከ 22 የምርጫ ጣብያዎች የተገኘው ቀዳሚ ውጤት፣ ፕረዚዳንት አልፋ ኮንዴ እየቀደሙ መሆናቸውን ያመለክታል። በሀገሪቱ ያሉት ተቃዋሚዎች ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል የተካሄደው ምርጭ ንዲሰረዝ እየጠየቁ ነው። ሁለት ዋና ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው ሄደት አግልለዋል።

የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ግን፣ በምርጫው ሂደት ያየነው ፣ የማጭበርበር ተግባር የለም ብለዋል። ይሁንና የምርጫ ጣብያዎችን፣ ዘግይቶ መክፈትና የመራጮችን አመዘጋገብ በተደራጀ መልክ አለማክሄድን የመሳስሉ ችግሮች እንደነብሩ ታዛቢዎቹ ጠቁመዋል። እንዚህ ችግሮች ድምጽ የሚሰጡት ዜጎች፣ ሰልፍ ላይ ባዙ እንዲቆዩ ማድረጋቸውንም አስገንዝበዋል።

እስማዔል ሲላ የተባለ ተማሪ፣ የሰጠሁት ድምጽ ተቆጥሮ እንደሆነ የንምተማመነው በ 80 ከመቶ ብቻ ነው ብሏል።

ከምርጫው በፊት ብዙ የምርጫ ካርዳቸውን ያላገኙ ሰዎች እንደንበሩ አውቃለሁ ነው የሚለው ተማሪው። በዚህ የምርጫ ጣብያ ላይ፣ ሰዎች ድምጽ ለመስጠት እስከምሽቱ ሶስት ሰአት እንደቆዩ ሲላ ገልጿል።

የሆቴል ዘበኛ ሲላ ፈጢማ ደግሞ ከሶስት አመታት በፊት ከተካሄደው የምክር ቤት ምርጫ ጋር ሲወደደር፣ የአሁኑ ምርጫ አያረካም ይላል።

ባለፈው እሁድ በተካሄደው ምርጫ ሰዎች የምርጫ ካርዳቸውን በጊዜ ስላላገኙ ለመምረጥ ቀላል አልነበረም ብላለች ፋቲማ። ለወደፊቱ የምርጫው ኮሚሽን ከዚህ በተሻለ መዘገጀት ይኖርበታል ስትልም አሳሳባለች።

የምርጫው ኮሚሽን ቃል-አቀባይ ሃሳብ እንዲሰጡበት ተሚክሮ አልተገኙም።

የአአሮፓ ህብረት ባደረገው የቅድሚያ ግምገማ፣ የሀገሪቱ ገዦ ፓርቲ ባለስልጣኖች፣በምርጫ ዘመቻ ላይ የምንግስትብን ሃብት ተጠቅመዋል ይላል። ይህ ደግሞ የምርጫው ህግን እንደሚጥስ ጠቁሟል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ ፕረዚዳንት ኮንዴ የመርቃጮችን ድምጽ ለማግኘት ገንዘብ አድለዋል ሲሉ ከሰዋል። የፕረዚዳንቱ ፓርቲ ቃል አቀባይ አህመት ትራኦሬ ግን፣ ፕረዚዳንቱ ማህበሰቦችን ሲጎበኙ፣ ገንዘብ የመስጠት ልምድ አላቸው። ሆኖም የመራጮችን ድምጽ ሊያስለውጥ የሚችል ያህል አይደለም ብለዋል።

ዘጋብያችን ክሪስ ስታይን ከኮናክሪ የላከውን ዘገባ አዳነች ፍሰሃየ አቅርባዋለች ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

ጊኒ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደውን ዲምክራስያዊ የሆነ የፕረዚዳንታዊ ምርጫ /ርዝመት - 2ደ33ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:33 0:00

XS
SM
MD
LG