በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግሪክ ከሰጠመችው ጀልባ ጋራ በተያያዘ ዘጠኝ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለች


ግሪክ ከሰጠመችው ጀልባ ጋራ በተያያዘ ዘጠኝ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለች
ግሪክ ከሰጠመችው ጀልባ ጋራ በተያያዘ ዘጠኝ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለች

በግሪክ፣ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ፣ በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል ከሚገኝ ባሕር ከሰጠመችው እና 78 ተሳፋሪዎች ከሞቱባት ጀልባ ጉዳይ ጋራ በተያያዘ፣ ዘጠኝ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጠ።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን በማዘዋወር እና በወንጀል ሥራ ተሳትፋችኋል፤ በሚል ነው። 750 ሰዎች፣ ተጨናንቀው ሳይሳፈሩበት እንዳልቀረ ከተገመተችው እና በማዕበል ተመትታ ከተገለበጠችው የዓሣ ማስገሪያ ጀልባ፣ እስከ አሁን 104 ሰዎችን በሕይወት እንደታደጉ፣ ዓለመቀፍ የፍልሰት ጉዳይ ድርጅት(IOM) አስታውቋል።

አሶሺዬትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ በሕይወት ከተረፉት ውስጥ፣ 27ቱ ወደ ሆስፒታል ተወስደው በመረዳት ላይ ናቸው።

በሌላ ዜና፣ ከአደጋው ከተረፉት አንዳንዶቹ በደረሰባቸው ከፍተኛ የአእምሮ መናወጥ የተነሣ፣ አሁንም ራሳቸውን ከጀልባ ላይ እንዳሉ እንደሚቆጥሩና የሚሞቱ መስሎ እንደሚሰማቸው፣ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG