በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለትግራይ ክልላዊ መንግሥት መግለጫ የፌዴራል መንግሥቱ ምላሽ


የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ የሰነዘረውን ትችት በስሜትና በቁጣ የተሞላ ሲሉ የገለፁት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ//ቤት የፕሬስ ክፍል ኃላፊ ንጉሡ ጥላሁን አሁን ለመጣው ለውጥ ምክንያቱ ከዚያ በፊት ይፈፀም የነበረው ግፍ ነው ብለዋል።

ክልሉን የሚመራው ቡድን እንደዚህ ዓይነት መግለጫዎችን የሚያወጣውም በዚያው በትግራይ እየተነሳ ያለውን ጥያቄ አቅጣጫ ለማስቀየርነው ሲሉም አቶ ንጉሡ ተናግረዋል።

በተዘረፈ ኃብትና ንብረት ኢትዮጵያ የስጋት ቀጠና እንድትሆን ከመስራት መታቀብ እንደሚሻልም አሳስበዋል፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የፕሬስ ክፍል ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በመግለጫው ላይ ምላሽ እንዲሰጡ አነጋግረናቸዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለትግራይ ክልላዊ መንግሥት መግለጫ የፌዴራል መንግሥቱ ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:11 0:00


XS
SM
MD
LG