ዋሽንግተን ዲሲ —
በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ ከቃጠሎ የተረፈውን የገበያ ቦታ እና ሌሎች ንብረቶችን ሊያቃጥሉ ነበር ያሏቸውን ግለሰቦች መያዛቸውንና ለፖሊስ ማስረከባቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ። በጎንደር ተጨማሪ የቃጠሎ አደጋ ይደርሳል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ገልጸዋል።
የክልሉ መንግስት በበኩ እንደተባለው ሁለት ወጣቶችን ሕብረተሰቡ ይዞ ለሕግ እንደሰጣቸው ገልጾ ግለሰቦቹ ንብረት ወደማውደም የሚያመራ ነገር ይኑራቸው አይኑራቸው የሚለውን ለማጣራት ምርመራ እየተደረገ ነው ብሏል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።