No media source currently available
በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ ከቃጠሎ የተረፈውን የገበያ ቦታ እና ሌሎች ንብረቶችን ሊያቃጥሉ ነበር ያሏቸውን ግለሰቦች መያዛቸውንና ለፖሊስ ማስረከባቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ። በጎንደር ተጨማሪ የቃጠሎ አደጋ ይደርሳል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ገልጸዋል።