በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት


አቶ ታማኝ በየነ
አቶ ታማኝ በየነ

በዓለም ዙሪያ ችግር ላይ ለሚወድቁ ኢትዮጵያዊያን ፈጥኖ ለመድረስና ለመብቶቻቸው መከበር እንደሚሠራ የሚናገረው “ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት” የሚባል ስብስብ የፊታችን ነኀሴ 6 ወይም ኦገስት 12 ዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለሚኖሩ ዝግጅት አሰናድቷል።

በዓለም ዙሪያ ችግር ላይ ለሚወድቁ ኢትዮጵያዊያን ፈጥኖ ለመድረስና ለመብቶቻቸው መከበር እንደሚሠራ የሚናገረው “ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት” የሚባል ስብስብ የፊታችን ነኀሴ 6 ወይም ኦገስት 12 ዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለሚኖሩ ዝግጅት አሰናድቷል።

ግሎባል አልያንስ
ግሎባል አልያንስ

​የዝግጅቱ ሃሣብ ቡድኑ በየቦታው ላሉ ኢትዮጵያዊያን ለሚሰጣቸው ደራሽ ድጋፎች “ከእሣት አደጋ ሩጫ” ይልቅ ይበልጥ በተደራጀ ሁኔታ ለመዘጋጀት አቅምን ለማጠናከር እንደሆነ የትብብሩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ታማኝ በየነ ለቪኦኤ ገልጿል።

ቡድኑ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ መሆኑንና ከፖለቲካም ውጭ መሆኑን ያመለከተው አቶ ታማኝ የኢትዮጵያ መንግሥት ፍቃደኛ ሆኖ ከተገኘ በበርካታ የወገንና የሃገር ቤት ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት ትብብሩ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

የፊታችን ኦገስት 12 ወይም ነኀሴ 6 ሲልቨር ስፕሪንግ፤ ሜሪላንድ በሚገኘው ዳብል ትሪ ሆቴል ከአምስት ፒኤም ጀምሮ በሚካሄደው ዝግጅት ላይ በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንዲገኙና ድጋፍ እንዲሰጡ፣ ሌሎችም ወደ ዌብሳይቱ ‘globalalliancefortherightsofethiopians.org’ ወይም ‘defendethiopians.org’ ገብተው እንዲሣተፉ፣ እንዲደግፉና በገንዘብም እንዲረዱ አቶ ታማኝ ጠይቋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:15 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG