በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የእጅ ቦምብ ሁለት ሰው ገደለ


በዲላ ዩኒቨርሲቲ
በዲላ ዩኒቨርሲቲ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትናንት፤ ሐሙስ ምሽት ላይ በተጣለ አደጋ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት መጥፋቱ ተዘገበ፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትናንት፤ ሐሙስ ምሽት ላይ በተጣለ አደጋ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት መጥፋቱ ተዘገበ፡፡

በተጨማሪም ስድስት ተማሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና የአራቱ ጉዳት ከባድ መሆኑን እጅጉ ሺፈራው የሚባሉ የዲላ ከተማ የፖሊስ መኮንን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መናገራቸውን ሮይተርስ አመልክቷል፡፡

ሮይተርስ የፖሊስን መረጃ ጠቅሶ ባሠራጨው ዘገባ አደጋ ጣዮቹ የእጅ ቦምቦቹን ተማሪዎቹ ላይ ወርውረዋል፡፡

የጥቃቱ ምክንያት አልተገለፀም፤ ኃላፊነት የወሰደም ወገን የለም፡፡

እስከአሁን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ሰዎች መኖራቸው ከመገለፁ ሌላ የወጣ ዝርዝር ማብራሪያ የለም፡፡

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የጌዶዖ ዞን ማዕከል የሆነችው ዲላ ከአዲስ አበባ 350 ኪሎ ሜትር በስተደቡብ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡

XS
SM
MD
LG