በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአንዋር ቦምብ ፈነዳ


አንዋር መስጊድ እና አካባቢው፤ ዓርብ፣ መስከረም 25/2005 ዓ.ም
አንዋር መስጊድ እና አካባቢው፤ ዓርብ፣ መስከረም 25/2005 ዓ.ም

በአዲስ አበባ አንዋር መስጂድ ላይ ዛሬ ከቀትር በኋላ የተጣለ ፈንጂ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ አንዋር መስጂድ ላይ ዛሬ ከቀትር በኋላ የተጣለ ፈንጂ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል፡፡

በፍንዳታው የሞተ ሰው እንደሌለ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች /ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳን ጠቅሰው የኢትዮጵያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ብሄራዊ የመረጃና የደኅንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ ፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል አምስት ሰው በጠና መጎዳቱንና ሌሎች 19 ሰዎች ቀላል እንደደረሰባቸው አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ምርመራና ክትትል እየተካሄደ መሆኑን ግብረ ኃይሉ መጥቀሱ ተዘግቧል፡፡

ቪኦኤ ያናገረው አንድ እማኝ ለጁምዓ ሶላት እዚያው አንዋር መስጂድ እንደነበረ ጠቅሶ ፍንዳታው የደረሰው ሶላቱ ካበቃ በኋላ ምዕመናኑ እየዘመሩና ከረሜላ እየበተኑ በነበረ ወቅት አንድ በሶፍት ወረቀት የተጠቀለለ ትንሽ ነገር ከከረሜላዎቹ ጋር አብሮ ወደላይ ሲወረወር እንደሆነ በሥፍራው የነበሩ ጓደኞቹ እንደነገሩት ገልጿል፡፡

ፖሊስ አካባቢውን ወዲያው እንዳጠረ የገለፀው ይኸው እማኝ ለምሽቱ ሶላት ከሰዓት በኋላ አሥር ሰዓት አካባቢ ወደ መስጂድ ሲመለስ ፍንዳታው የደረሰበት ቦታ ላይ ደምና ጥቂት የቁርጥራጭ አካል ቅሪቶችን ማየቱን ተናግሯል፡፡

ከአደጋው ጋር የተያያዘ እሥራት አልተካሄደም ወይም ተጠርጣሪው ማን እንደሆነ እስከአሁን አልተገለፀም፤ አደጋውን የጣልኩ እኔ ነኝ ያለም የለም፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በአንዋር ቦምብ ፈነዳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:41 0:00

XS
SM
MD
LG