ዋሺንግተን ዲሲ —
የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ውዝግብ በአካባቢያዊ ተቋም እንዲያዝ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ወደ አፍሪካ ኅብረት ከመራው በኋላ የተካሄደው ድርድር ያለስምምነት መቋረጡ ተዘግቧል።
ድርድሩ እየተካሄደ ሳለ የውጡ የሳተላይት ምስሎች ግድቡ ውኃ እየያዘ መሆኑን ሲያሳዩ የታቆረው ውኃ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተፈጥሯዊ ሁኔታ የተያዘ መሆኑንና ይህም እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና የኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ አሳውቀዋል።
ተከታዩ ዘገባ በግድቡ ላይ እየተከናወነ ያለውን፣ በቅርቡ የነበሩ የውዝግብ ሂደቶችና የአሁን አያያዝም ይዳስሳል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።