በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋምቢያ መንግስት በሰላማዊ ተቃውሞ ላይ ጥቃት ከፈተ ሲል አንድ የዳያስፖራ ቡድን ከሰሰ


ፋይል ፎቶ - የጋምቢያው የፕረዚዳንት ያህያ ጃሜ
ፋይል ፎቶ - የጋምቢያው የፕረዚዳንት ያህያ ጃሜ

የጋምቢያ ዲያስፖራ ማለት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ጋምቢያውያን የፕረዚዳንት ያህያ ጃሜ መንግስት ሰላማዊ ተቃውሞ ያካሄዱ በነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃት በመክፈት የጋምቢያውያን መሰረታዊ ሰብአዊ መብትና ህገ-መንግስታዊ መብትን ረግጠዋል ሲሉ ይከሳሉ። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ጋምቢያውን ዲሞክራስያዊ ህብረት የተባለ ቡድን ቃል አቀባይ ፒኤ ሳምባ ጃዎ የጋምቢያ ህገ-መንግስት ሰላማዊ ተቃውሞ የማካሄድ መብት ይፈቅዳል ብለዋል።

ፒኤ ሳምባ ጃዎ (PA Samba Jow) መንግስት ሳሎ ሳንዴንግ እና ሌሎች በጸጥታ ሃይሎች ተገደለዋል የሚባሉትን ሰዎች እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። እስካሁን ባለው ጊዜ ግልጽ የሆነ ነገር እንደሌለ ጆው ጠቁመዋል።

“የጋምቢያ መንግስት እስካሁን ባለው ጊዜ የስሎ ሳንዲንግንና ሌሎች ሁለት ተገደሉ ወይም ኮማ ላይ ናቸው የተባሉ ሰዎችን አስከሬን ለማቅረብ አልቻለም። ሁሉም የተባበረው ዲሞክራስያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው። በአሁኑ ወቅት የተባበረው ዲሞክራስያዊ ፓርቲ መሪ እስር ቤት ናቸው። ከማንም ጋር ለመገናኘት አይፈቀድላቸውም። የት እንደታሰሩ አናውቅም። መንግስትም ስለሳቸው የተናገረው ነገር የለም።”ብለዋል።

ፒኤ ሳምባ ጃዎ አያይዘውም ትላን 24 ሰዎች እንደታሰሩ ባለፈው ሀሙስ ደግሞ 13 ሰዎች እንደተያዙ ጠቁመዋል። 13 ቱ የታሰሩት የምርጫ ለውጥ እንዲደረግ ሰላማዊ ተቃውሞ በጀመሩበት ወቅት ነው ይላሉ የዲያስፖራው ቡድን ቃል አቀባይ።

የጋምቢያ ማስታወቅያ ሚኒስትር በበኩላቸው የተገደሉ ሰዎች ካሉ እየተጣራ እንደሆነ ገልጸው የታሰሩት ፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

እኛ ጋምቢያውያን እነዚህ ሰዎች ነጻ እንዲወጡ ብቻ ሳይሆን ለተፈጸመው ሁሉ ተጠያቂነት እንዲኖር ለመታገል ቆርጠን ተንስተናል። እንዲሁም ለ 22 አመታት ለሚጠጋ ጊዜ የቆየውን የጭካኔ አገዛዝ ማብቂይ ሊጀምር ለሚችል ትግል ቆርጠን ተነስተናል ብለዋል።

የጋምቢያ የማስታወቅያ ሚኒስቴር በበኩላቸው ተቃዋሚዎቹ ከሚመለከተው ክፍል ፈቃድ ሳያገኙ የተቃውሞ ሰልፍ በማክሄድ ሕግ ጥሰዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ፒኤ ሳምባ ጃዎ ግን የሀገሪቱ ህገ-መንግስት ማንኛውም ጋምቢያዊ ሰላማዊ ታቃውሞ የማካሄድ መብት እንዳለው በግልጽ አስቀምጦታል ይላሉ። ዋናው ነገር ግን እንዚህ ሰዎች ለእንደዛ አይነት ጭካኔ ለተመላበት ጥቃት ሊዳርጋቸው የሚችል የፈጸሙት ነገር የለም ሲሉ አስገንዝበዋል።

ሀግ የጣሰ ክፍል ካለ በሰላማዊ ተቃውሞ ላይ ጥቃት የከፈቱት መንግስትና የጸጥታ ሃይሎች ናቸው ብለዋል። የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ የከፈቱትና እምባ አስምጪ ጋዝ የተጠቀሙት መፍክር ብቻ በያዙ ሰዎች ላይ ነው ሲሉ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ጋምቢያውን ዲሞክራስያዊ ህብረት የተባለ ቡድን ቃል አቀባይ ፒኤ ሳምባ ጃዎ ገልጸዋል።

የእንግሊዘኛው ክፍል ዘጋቢ ጀምስ ባቲ ቃል አቀባዩን አነጋግሮ የላከውን ዘገብ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የጋምቢያ መንግስት በሰላማዊ ተቃውሞ ላይ ጥቃት ከፈተ ሲል አንድ የዳያስፖራ ቡድን ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG