በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ከ20 ቀናት በፊት ባጋጠመ ግጭት ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ 11ሺሕ ሰዎች፣ እስከ አሁን ርዳታ አለማግኘታቸው ተገለጸ፡፡
የተፈናቃዮቹን ኹኔታ አስመልክተው ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ተፈናቃዮቹ ከ20 ቀናት በላይ ለኾነ ጊዜ፣ የምግብ እና የመጠለያ ርዳታ ስላላገኙ ለችግር መዳረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ የጋምቤላ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ቢሮ በበኩሉ፣ “ተፈናቃዮቹ በቅርቡ ርዳታ ይደርሳቸዋል፤” ብሏል፡፡
መድረክ / ፎረም