በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን-7 ዓባል ሃገራት አንድ ቢሊየን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመለገስ ቃል ገቡ


በትናንትናው ዕለት በብሪታኒያ ኮርንወል ዛሬ የሚካሄደው የቡድን ሰባት አባል ሃገራት መክፈቻ ላይ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን ቡድኑ 1 ቢሊየን የኮቪድ 19 ክትባቶችን መሃከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሃገራት እንደሚለግስ አስታውቀዋል፡፡

ቦሪስ ይህን ያሉት ቀን ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ለቡድን ሰባት አባል ሃገራት የመዋጮው ግማሽ የሚሆነውን 500 ሚሊየን የሚሆኑ የፋይዘር ክትባቶችን እንለግሳለን ካሉ በኋላ ነው፡፡ ፕሬዘዳንቱ “ከዓለም አቀፍ አጋሮቻችን ጋር በመስራት ዓለም ከወረርሽኙ እንዲወጣ እንመራለን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ብሪታኒያም 100 ሚሊየን ክትባቶችን ትለግሳለች፡፡

ቦሪስ፤ “በተሳካው የክትባት መርሃግብር ምክንያት አሁን ላይ ክትባት ለሚሹ ሃገራት ማጋራት የምንችለው ብዙ ክትባት አለን” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “ይህንን በማድረጋችንም ወረርሽኙን ጨርሶ ለማጥፋት ትልቅ እርምጃ ተራምደናል፡፡” ብለዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ከመጪው ነሃሴ ወር ጀምሮ ክትባቶቹን መላክ ትጀምራለች ያሉት ባይደን “አምራች ድርጅቱ ክትባቶቹን እንደለቀቀ በቶሎ ይላካሉ” ብለዋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ አክለውም 200 ሚሊየን ክትባቶች እስከ ጎርጎሮሳዊያኑ 2021 ማብቂያ 300 ሚሊየኑ ደግሞ በቀጣይ በ2022 ዓ.ም እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ ባይደን ልገሳው በልዋጩ ምንም የሚጠይቀው ነገር እንደሌለም ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ቀሪዎቹ የቡድን 7 አባል ሃገራት ምን ያህል ክትባት እንደሚያዋጡ የታወቀ ነገር ይለም፡፡ አብዛኞቹ ሃገራትም ክትባት ለህዝባቸው ማካፈሉ ላይ በተለያየ አቋም ላይ ያሉ ሲሆን ጃፓን እና ካናዳ እስካሁን ድረስ 10 በመቶ የሚሆነውን ህዛባቸውን ብቻ በማዳረሳቸው ለጋሽ ለመሆነ የሚያችላቸው አቋም ላይ አይደሉም፡፡

በዚህ ቃልኪዳን አማካኝነትም ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም ክትባት በማግበስበስ ከደረሰባት ወቀሳ የመላቀቅ ዓላማ አላት፡፡

XS
SM
MD
LG