ዋሽንግተን ዲሲ —
የፈረንሳይ ፕረዚዳንት ፍራንሷ ኦላንድ ዛሬ ለሀገሪቱ ባደረጉት ንግግር ድርጊቱን በነጻነት ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው ብለውታል። “በፈረንሳይ ላይ ጥቃት የተከፈተው በትላንቱ ሐምሌ 14 ቀን የነጻነት ተምሳሌት የሆነው ብሔራዊ ዕለት በሚከበርበት ወቅት ነው። ጽንፈኞች ሰብአዊ መብትን የሚነፍጉ በመሆናቸው ፈረንሳይ ኢላማ መደረግዋ አይቀርም።”ብለዋል።
ሆላንድ ባለፈው ህዳር ወር ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት ያወጁትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደገና በሦስት ወራት እንዲራዘም አዘዋል። ዛሬ የመከላከያ መማክርት ስብሰባ ከጠሩ በኋላ ወደ ኒስ ሄደዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ዛሬ ማለዳ ከሩስያው አቻቸው ጋር ሞስኮ ላይ ስብሰባ በሚያከሄዱበት ወቅት፤ “በኒስ የተፈጸመው ጥቃት አሸባሪነትን ለመታገል አለም አቀፍ ጥረት ማፋጠን እንዳለብን ያሳያል” ብለዋል።
ዘጋቢያችን Jeff Custer ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።