በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

14 የደቡብ ሱዳን ወጣቶች የወጣት አፍሪቃውያን መሪዎች መርሓ-ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጠ


ፋይል ፎቶ - ባራክ ኦባማ በዋሽንግተን ዲሲ የወጣት አፍሪቃውያን መሪዎች መርሓ-ግብር ላይ ከተሳታፊዎች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች እየመለሱ እ.አ.አ.2015
ፋይል ፎቶ - ባራክ ኦባማ በዋሽንግተን ዲሲ የወጣት አፍሪቃውያን መሪዎች መርሓ-ግብር ላይ ከተሳታፊዎች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች እየመለሱ እ.አ.አ.2015

ተመራጮቹ ወጣቶች በቀጣዩ ሳምንት ወዲህ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ጉዞ ይጀምራሉም ተብሏል።

በፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በተጀመረው የወጣት አፍሪቃውያን መሪዎች መርሐ-ግብር፣ 14 የደቡብ ሱዳን ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገለጠ።

ተመራጮቹ ወጣቶች በቀጣዩ ሳምንት ወዲህ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ጉዞ ይጀምራሉም ተብሏል። ከዚያም በተለያዩ እንደ ንግድ አስተዳደር፣ ሲቪክ አመራርና ሕዝባዊ አስተዳደር ለመሰሉ ስልጠናዎች ወደ አሜሪካ ዩኒቨርሲቲና ወደ ሌሎችም ኮሌጆች ይላካሉ።

አሥራ-አራቱ የደቡብ ሱዳን ወጣቶች፣ ከሌሎች የአፍሪቃ አገሮች ከሚውጣጡ ወደ 1,000 ያህል ወጣቶች ጋር ተደባልቀው የስልጠናው መርሓ-ግብር ተካፋዮች እንደሚሆኑም ታውቋል።

ጁባ የሚገኘው የየዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የመረጃ ዳይሬክተር ክሪስ ማዴ እንደገለጹት፣ ሰባቱ ወንዶችና ሰባቱ ሴቶች የተመረጡት፣ ከ400 ተወዳዳሪዎች መካከል ነው።

የሁሉም አመልካቾች ዕድሜ ከ25-35 ዓመት መሆኑን የገለጹት ማዴ ከዚህ ቀደም ማናቸውም ዩናይትድ ስቴትስ መጥተው የማያውቁ እንደሆኑ ነው የተናገሩት።

ከዚህ በፊት በወጣቶች መርሐ-ግብር ላይ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈው ነበር። ያነጋገርናቸውን ወጣቶች ቪድዮዎች ከዚህ በታች ይመልከቱ።

ከያሊ ምን ተማራችሁ? ወጣት ኢትዮጵያዊያንንስ እንዴት ይረዳል?

ከያሊ ምን ተማራችሁ? ወጣት ኢትዮጵያዊያንንስ እንዴት ይረዳል?
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:34 0:00

በቡና የውጭ ሽያጭ ላይ የተመሰረተ ቢስነስ አለሽ። ይህንን ንግድ ለማሳደግ ከያሊ ምን አግኝቻለው ትያለሽ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:46 0:00

መሪዎች ናችሁ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:53 0:00

XS
SM
MD
LG