በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ራቁቴን ተገርፌያለሁ” - አሸናፊ አካሉ


ከአምስት አመት ተኩል እስር በኋላ ቅዳሜ ዕለት ከእስር የተፈታው አሸናፊ አካሉ።
ከአምስት አመት ተኩል እስር በኋላ ቅዳሜ ዕለት ከእስር የተፈታው አሸናፊ አካሉ።

አሸናፊ አካሉ በምዕራብ ጎጃም ሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ ውስጥ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት የግዢ ኃላፊ በነበረበት ወቅት በሽብር ወንጀል ተከሶ መታሰሩን ይናገራል። በእስር ላይ በነበረበት ወቅትም አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈፀመበት ይናገልፃል።

በተለያዩ የወንጀል ሕጎችና አንቀፆች ተከሰውና ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የነበሩ በዐስር ሺዎች የተቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች ከኢትዮጵያ እስር ቤቶች መፈታት ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል።

ባሳለፍነው አርብና ቅዳሜ በዩኒቨርስቲ ትምሕርትና በሥራ ላይ የነበሩ ወጣቶች ከእስር ተለቀዋል።

እነዚህ ከእስር የተለቀቁት ወጣቶች እስር ቤት ውስጥ የነበራቸው የአያያዝ ሁኔታ ሰብዓዊ መብታቸውን በእጅጉ የጣሰና በምርመራ ወቅት ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እደተፈፀመባቸው እየገለጹ ነው።

ወጣቶቹ ከእስር መፈታት በኋላ ስለሚኖራቸው ሕይወት የተወሰኑትን ጠይቀናቸዋል። በትናንትናው ምሽት ዘገባችን ከፍያለው ተፈራ ስለተባለው ሁለት እግሮቹን ስላጣው ወጣት ታሪክ ዘገባ አቅርበን ነበር።

ዝግጅቱን ያጠናቀረችው ጽዮን ግርማ ለዛሬ አሸናፊ አካሉ ስለተባለ ከአምስት አመት ተኩል እስር በኋላ ቅዳሜ ዕለት ከእስር ስለተለቀቀ የ34 ዓመት ወጣት ታሪክ አጠናቅራለች።

ሙሉውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“ራቁቴን ተገርፌያለሁ” - አሸናፊ አካሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:12 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG