ዋሽንግተን ዲሲ —
አምስቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ቡድኖች፥ የቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃ አውጪ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝብ ነፃ አውጪ ንቅናቄ፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርና የሲዳማ ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር መሆናቸው ተገልጿል።
በተቃዋሚዎቹ መግለጫ መሠረት አዲሱ ሕብረት፣ ጨቋኝ የሚሉትን የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማራም ደሳለኝ መንግሥት ለመለወጥና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች የሽግግር ሥርዓት ለመመስረት ያስችላል።
አቶ ቶሌራ አደባ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸው። ግንባሩን ወክለው በኦስሎው ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል።
ሰሎሞን ክፍሌ በስልክ አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ ለመስማት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ይጫኑ።