በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ከኢምፓየሯ ምንም ዓይነት ስጦታ/ገጸ-በረከት አንሻም" - ፊደል ካስትሮ

ፋይል ፎቶ - ፊዴል ካስትሮ ሃቫና ኩባ ወስጥ እ.አ.አ 2015
ፋይል ፎቶ - ፊዴል ካስትሮ ሃቫና ኩባ ወስጥ እ.አ.አ 2015

የኰሙውኒስት አገራቸውን አመራር እ.አ.አ. በ2008 ለታናሽ ወንድማቸው ራውል (Raul) የሰጡት የ89 ዓመቱ ካስትሮ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ያቺን አገር ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት ሲጎበኙ አንዴም እንዳልተገናኙ ይታወቃል።

አረጋዊው የኩባ አብዮተኛ ፊደል ካስትሮ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለተጀመረው የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ደንታ እንደሌላቸው በማመልከት፣ "ከኢምፓየሯ ምንም ዓይነት ስጦታ/ገጸ-በረከት አንሻም" ማለታቸው ተሰማ።

የኰሙውኒስት አገራቸውን አመራር እ.አ.አ. በ2008 ለታናሽ ወንድማቸው ራውል (Raul) የሰጡት የ89 ዓመቱ ካስትሮ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ያቺን አገር ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት ሲጎበኙ አንዴም እንዳልተገናኙ ይታወቃል።

አንድ በሥልጣን ላይ ያለ የአሜሪካ መሪ ኩባን በ90 ዓመት ውስጥ ሲጎበኝ፣ ኦባማ የመጀመሪያው ናቸው።

ፕሬዚደንት ኦባማ፣ በጉብኝታቸው ወቅት፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ለ50 ዓመታት የዘለቀው መለያየት መቆም እንዳለበት ይፋ አድርገዋል።

ፕሬዚዳንት ኦባማ ከ 90 ዓመታት በኋላ ኩባን ለመጀመሪያ ጊዜ እየጎበኙ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:08 0:00

XS
SM
MD
LG