ሃያ ስምንት አፍሪካውያን ሴት ፍልሰተኞች ትላንት ከሊብያ እሥር ቤት ሲፈቱ የአሥራ ሁለት ዓመት ዕድሜ ህፃናትም ይገኙበታል፡፡
“እስላማዊ መንግሥት ነኝ” በሚለው ቡድን የተያዙት ፍልሰተኞች ፅንፈኛው ቡድን ሰርቴ ከተማን እአእ በ2015 መጨረሻ በወረረበት ወቅት ነበር።
አምስት ህፃናት ሴት ፍልሰተኞች ከእሥር የለቀቁት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፈው የሊብያ መንግሥት ወታደሮች ናቸው።
ወታደሮቹ ፅንፈኛውን ቡድን አምና ከአካባቢው ካስወጡ በኋላ የስደተኞች አገልግሎቶች የመፈታታቸውን ጉዳይ እስከሚያመቻቹበት ጊዜ ድረስ በሚስራታ እሥር ቤት እንደነበሩ ተገልጿል።
ከእስር የተፈቱት ሴቶች አብዛኞቹ ኤርትራውያንና ናይጀርያውያን መሆናቸው ታውቋል።
የዓለምቀፍ ቀይ ጨርቃ ባለሥልጣን ስልሕ ዐቡ-ዘሪባ ታሥረው የነበሩት ሴቶች እንዴት እንደተፈቱ ገልፀዋል።
“ዛሬ ከፍርድ ቤት ባለሥልጣኖችና ከዓለምቀፍ የፍልሠት ድርጅት /አይ ኦ ኤም/ ጋር በመተባበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡትን ሴቶች ለቀናል። አምስቱ ከናይጀርያ ሀያ ሦስቱ ደግሞ አምስት ልጆች የሚገኙባቸው ኤርትራውያን ናቸው። አሁን ለዓለምቀፍ የፍልሠት ድርጅት /አይ ኦ ኤም/ አስረክበናቸዋል። ድርጅቱ ወደ ሃገራቸው ይመልሳቸዋል።” ሲሉ እቡ ዘሪባ ገልፀዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ