በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተከሰከሰው የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 ጉዳይ!


“ሕግ አውጭዎቹ ያንን ዕድል .. የአደጋው ሰለባዎች ቤተሰብ አባላት የምስከርነት ቃል ለመስማት መፍቀዳቸው .. ስለተፈጠረው አደጋ ምንነትና የተጎጂው ቤተሰቦች ስላሉበት ሁኔታ እንዲያውቁ ይረዳቸዋል፤ ብዬ አምናለሁ።” አቶ ዘካሪያስ አስፋው - በአደጋው ወንድማቸውን ያጡ። “..ዳግም ይህን መሰል አደጋ እንዳይከሰት ለሚደረጉ ጥረቶች ያግዛል።..” አቶ ሼክስፒር ፈይሳ - የሕግ ባለሞያ

የበረራ ቁጥር 302 ጉዳይ፣ የUS ምክር ቤት እና የተጎጂ ቤተሰቦች ምላሽ!

ባለፈው መጋቢት ወር ከአዲስ አበባው የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ገና ብድግ ባለ ስድስት ደቂቃዎች ውስጥ በተከሰከሰውና ለ157ቱ ተሳፋሪዎቹ እልቂት ምክኒያት የሆነው የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ቦይንግ 737 Max ጉዳይ አሁንም እያነጋገረ ነው።

የአደጋው ሰለባዎች ቤተሰብ አባላት በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ተገኝተው የሰጡትን የምስክርነት ቃል አንድምታ በአንድ የተጎጂ ቤተሰብ አባልና የሕግ አማካሪያቸውን ምላሽ ይዟል።

የአውሮፕላኑ አምራች ኩባንያ ቦይንግ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ እና በኢንዶኔዥያው ዓየር መንገድ ተመሳሳይ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች መርጃ “አንድ መቶ ሚልዮን ዶላር እሰጣለሁ” ያለበትን ዜናም ይመዝናሉ።

ምላሾቹን የሰጡት በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በረራ ቁጥር E-302 ቦይንግ 737 Max ወንድማቸውን ያጡት አቶ ዘካሪያስ አስፋውና የሕግ አማካሪያቸው አቶ ሼክስፒር ፈይሳ ናቸው።

ተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የበረራ ቁጥር 302 ጉዳይ፣ የUS ምክር ቤት እና የተጎጂ ቤተሰቦች ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:33 0:00
የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ ስምንት ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:57 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG