በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ


የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከልና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በቻንስለሯ የኢትዮጵያ ጉብኝት ወቅት
የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከልና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በቻንስለሯ የኢትዮጵያ ጉብኝት ወቅት

የአውሮፓ ኅብረትና ዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ ሂዩማን ራይትስ ዋች የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ዛሬ ጥሪ አሰምቷል፡፡

የአውሮፓ ኅብረትና ዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ ሂዩማን ራይትስ ዋች የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ዛሬ ጥሪ አሰምቷል፡፡

ቡድኑ መልዕክቱን ያስተላለፈው በአውሮፓ ኅብረት ንዑስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

“ሰብዓዊ መብቶችን የመርገጥና ሃሣብን በመግለፅ ነፃነት ላይ ገደብ መጣልን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን በተመለከተ ተወቃሿ ኢትዮጵያ ስትሆን ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጉዳዩን የሚመለከተው በአመዛኙ በተለየ አቅጣጫ መሆኑን ታዝበናል” ብሏል ዓለምአቀፉ የመብቶች ተሟጋች ቡድን፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ቃፊሩና ተሟጋቹ ቡድን ሂየማን ራይትስ ዋች ከፍተኛ መርማሪ ፌሊክስ ሆርን “ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ጠጠር ያሉ፣ ወይም የከበዱ ጉዳዮችን፣ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ጥያቄዎችን ለመንካት ያለመፈለግ አካሄድ እንዳለ እናምናለን” ብሏል ፡፡

“ምክንያቱም ይላል - ሆርን - ኢትዮጵያ በልማት፣ በፍልሰትና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ ከምትተባበራቸው ዓለም አቀፍ አጋሮቿ ጋር ጠንካራ ግንኙነቶች አሏት፡፡”

ሆርን በመቀጠል ″የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ላይ ይበልጥ የጠነከረ እርምጃ መውሰድ አለበት፤ ዓለምአቀፍ ምርመራ እንዲደረግ ግፊት ማሳደር አለበት፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፈታሾች መግባት እንዲፈቀደላቸው ግፊት ማሳደር አለበት፤ እስካሁን ምላሽ ያልተሰጣቸው አሥራ አንድ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በዘፈቀደ ይዛ ያጎረቻችውን ሁሉ እንድትፈታ የአውሮፓ ኅብረት ግፊት ማሳደር አለበት” ብሏል፡፡

ቤልዥክ ዋና ከተማ ብሩሴል ዛሬ በተቀመጠው የአውሮፓ ኅብረት የንዑስ ኮሚቴው ስብሰባ ላይ የተገኙ የኢትዮጵያ መልዕክተኛ ከተቃዎሚ ፓርቲዎችና ከሲቪል ማኅበረሰቦች ጋር ውይቶችን ለማድረግ ማረጋገጫ መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ1997 ዓ.ም አካሂዳ የነበረው አጠቃላይ ምርጫ ተዛቢ ሆነወ ከአውሮፓ ኅብረት ተልከው የነበሩት የአውሮፓ ፓርላማ አባል አና ጎምሽ የጀርመን መሪ አንጌላ መርከል ኢትዮጵያ መሄዳቸው እንዳሳዘናቸው ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:24 0:00

XS
SM
MD
LG