በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውሮፓ ኅብረት 8 ቢሊየን ዶላር ለግብፅ ሊሰጥ ነው


የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ፣ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ከኦስትሪያ መሪዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ተፈራርመው መግለጫዎች ሰጥተዋል፤ ይህ ምስል በግብፅ ፕሬዚዳንት ቢሮ የቀረበ ነው እአአ መጋቢት 17/2024
የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ፣ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ከኦስትሪያ መሪዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ተፈራርመው መግለጫዎች ሰጥተዋል፤ ይህ ምስል በግብፅ ፕሬዚዳንት ቢሮ የቀረበ ነው እአአ መጋቢት 17/2024

በአፍሪካ የበረታው የኢኮኖሚ ጫና እና ግጭቶች ወደ አውሮፓ የሚፈልሱ ስደተኞችን ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት የገባው አውሮፓ ኅብረት፣ የገንዘብ እጥረት ላጋጠማት ግብፅ የ8 ቢሊየን ዶላር የርዳታ ጥቅል እንደሚሰጥ አስታወቀ።

የርዳታ ስምምነቱ የሚፈረመው፣ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን እና የቤልጂየም፣ ጣሊያን፣ ኦስትሪያ፣ ቆጵሮስ እና ግሪክ መሪዎች ግብፅን በሚጎበኙበት ወቅት መሆኑን የግብፅ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ግብፅ የሚገኘው የአውሮፓ ኅብረት ተልዕኮ በበኩሉ፣ የርዳታ ጥቅሉ ከአረብ ሀገራት ትልቁን የሕዝብ ብዛት ለያዘችው ሀገር፣ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ የሚሰጥ ርዳታ እና ብድርን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጿል።

ግብፅ ከሚገኘው ተልኮ የተገኘው ሰነድ፣ ሁለቱ ወገኖች ትብብራቸውን ወደ "ስልታዊ እና ሁሉን አቀፍ አጋርነት" ደረጃ ከፍ ማድረጋቸውን እና ይህም ኢኮኖሚያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ባልሆኑ መስኮች የግብፅ እና የአውሮፓ ኅብረትን አጋርነት ለማስፋት መንገድ መጥረጉን አመልክቷል።

የአውሮፓ ኅብረት ርዳታውን የሚሰጠው፣ የግብፅ መንግሥት፣ በተለይ ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ድህነትን እና ግጭቶችን ለሚሸሹ ስደተኞች ዋና መሸጋገሪያ ከሆነችው ሊቢያ ጋራ ያለውን ድንበር እንዲያጠናክር እና፣ በሱዳን ለአንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የሚካሄደውን ጦርነት ሸሽተው የሚሰደዱ ሱዳናውያንን እንዲያስተናግድ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG