በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት ኀይሎቹ በመርዓዊ ግድያ መፈጸማቸውን አስተባበለ


የኢትዮጵያ መንግሥት ኀይሎቹ በመርዓዊ ግድያ መፈጸማቸውን አስተባበለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:19 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥት ኀይሎቹ በመርዓዊ ግድያ መፈጸማቸውን አስተባበለ

የኢትዮጵያ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ በሰሜን ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ቤት ለቤት እየተዘዋወሩና በጅምላ ሲቪሎችን ገድለዋል፤ በሚል የወጡ ሪፖርቶችን መንግሥት አስተባበለ።

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፣ “ሲቪሎችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ በመንግሥት ኃይሎች አልተፈጸመም፤” ሲሉ ውንጀላውን ተከላክለዋል፡፡

የቤተሰባቸው አባል መገደሉን ገልጸው አስተያየት የሰጡን ምንጮች በበኩላቸው፣ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰላማውያን ሰዎች የተገደሉት በመንግሥት ኃይሎች እንደሆነ ተናግረዋል።

መከላከያ ሠራዊቱ ርምጃ የወሰደው፣ “ጥቃት በፈጸሙበት ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ ነው፤” ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ሲቪሎችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ከተፈጸመ ተጣርቶ ርምጃ ይወሰዳል፤” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት ዲሬክተር መስዑድ ገበየሁም ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የሲቪሎች ግድያ አሳሳቢ እንደሆነ ጠቅሰው፣ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ በመርዓዊ ከተማ በርካታ ሲቪሎች በመንግሥት ኃይሎች እንደተገደሉ መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ኅብረት ጉዳዩ እንደሚያሳስባቸውና ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG