ዋሺንግተን ዲሲ —
ባለፈው ሰኔ ወር የወጣ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት የኤርትራ መንግሥት መሪዎች ከሃያ በላይ ዓመታት በፊት
“በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ ወንጀል ፈጽመዋል” ማለቱ ይታወሳል።
ከመርማሪው ኮሚሽን ሦስት አባላት አንዷ የነበሩትና የመጀመሪያዋ የመንግሥታቱ ድርጅት የኤርትራ ጉዳይ ልዩ ራፖርተር ሺላ ኪታሩት ለቪኦኤ እንዳሉት ኮሚሽኑ በሪፖርቱ የሰዎች ደብዛ ማጥፋት ማሰቃየት፣ ያለፍርድ ሄደት ላልተወሰነ ጊዜ በእስር ማቆየት፣ እንዲሁም ርሸናን ጨምሮ የተለያዩ ኢሰብዓዊ ተግባራት ስለመፈጸማቸው ማስረጃዎችን ዘርዝሮ አቀርቡዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያዳምጡ፡፡