በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌደራል ሥርዓቱና የኢትዮጵያ ፖለቲካ


ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ

ኅብረብሄር ፖለቲካ? ወይስ የብሔር-ብሔረሰቦች ፌደራሊዝም? - ውይይት ከአቶ ገለታው ዘለቀ ጋር፡፡

አቶ ገለታው ዘለቀ ያጠኑትና የድኅረ-ምረቃ ዲግሪ ያገኙበት መስክ ልማት ነው።

ከደቡብ ኮርያ ጓንጁ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ በልማት ጥናት ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው።

በኢትዮጵያ ወቅታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሣትፎ ያደርጋሉ። “የኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች” በሚል ርዕስ ለንባብ ያበቁትን ጹሑፍ መሠረት አድርገን ለውይይት ጋብዘናቸዋል።

አቶ ገለታው “በብሔር-ብሔረሰብ መደራጀትን የሚመርጡ ኢትዮጵያዊያን በሕገ-መንግሥቱ የተደነገገውን ገዥው ፓርቲ ባለማክበሩ እንጂ የፌዴራል ሥርዓቱ የምንመርጠው ነው” እንደሚሉ ይናገራሉ፡፡

ኅብረብሔር ሆነው የተደራጁ ደግሞ “ፌዴራል ሥርዓቱ ለሀገሪቱ ፖለቲካ መመሳቀል ምክንያት ነው” እንደሚሉ አቶ ገለታው ዘለቀ ይጠቁማሉ፡፡

በአመለካከት ወደ እነዚህኞቹ ወገን ያደላሉ፡፡

የሕወሓት መሥራችና ከፍተኛ የአመራር አባላትም በቅርቡ ኢትዮጵያን ከገጠማት ቀውስ ጋር አያይዝው ስለ ኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ሥርዓት የተናገሩት አለ፡፡

ሁለቱን ሃሳቦች የተጣቀሱበትን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ፌደራል ሥርዓቱና የኢትዮጵያ ፖለቲካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:24:03 0:00

XS
SM
MD
LG