በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች “በሳዑዲ አረቢያ ተገደሉ”


ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች “በሳዑዲ አረቢያ ተገደሉ”
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:15 0:00

ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች “በሳዑዲ አረቢያ ተገደሉ”

የሳዑዲ አረቢያ የወሰን ዘቦች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችንና ከለላ ጠያቂዎችን መግደላቸውን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ቡድን ህዩማን ራይትስ ዋች ዛሬ አስታውቋል።

ድንበር ጠባቂዎቹ በኢትዮጵያዊያኑ ላይ የመንና ሳዑዲ አረቢያ ድንበር ላይ ግድያውን የፈፀሙት ከመጋቢት 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ባስታወቀበት ሪፖርቱ አድራጎቱ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ቡድኑ ጠቁሟል።

እንዲህ ዓይነቱ በፍልሰተኞች ላይ ግድያ መፈፀም የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ፖሊሲ ከሆነ “በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል” ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች ጠርቶት የመንግሥታቱ ድርጅት ምርመራ እንዲያደርግ አሳስቧል።

የሳዑዲ ባለሥልጣናት ከዓለም ዕይታ በራቀው በዚያ አካባቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶችና ህፃናትን እየገደሉ የሃገራቸውን ገፅታ ለመገንባት በሚል ፕሮፌሽናል የጎልፍ ተጫዋቾችንና የእግር ኳስ ቡድኖችን በመግዛት እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን እንደሚያፈስሱ የተናገሩት የቡድኑ የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች መርማሪ ናዲያ ሃርድማን ይህ እንቅስቃሴያቸው ከሚዘገንኑት ወንጀሎች ትኩረት ሊሰርቁ አይገባም” ብለዋል።

73 ገፆች ያሉት ይህ የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት በተደራጀና በተዘጋጀ ሁኔታ እየተፈፀመ እንደሆነ የጠቆመውን በኢትዮጵያዊያኑ ፍልሰተኞችና ከለላ ጠያቂዎች ላይ እየተካሄደ ያለውን ጥቃት ማጉላላትና በደል በሰብዕና ላይ የተፈፀመውን ወንጀል ያልቀዋል” ብሏል።

በሪፖርቱ ላይ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ በሳዑዲ አረቢያ ድንበር ጠባቂዎች የደረሰባቸውን ጥቃት እንዲህ ገልጿል። ለደህንነታቸው ሲባል ቃሎቻቸው የተነበቡት በሌሎች ሰዎች ድምፆች ነው።

“መሽቶ ነበረ። ወደ ሳዑዲ ድንበር እየተጓዝን ነበር። የሳዑዲን የድንበር ጠባቂዎች አየናቸው። እንድንቆም አዘዙን። ከዛም ወደኛ እየቀረቡ መጡ። እየተራመዱ ይተኩሱብን ጀመር። አንድ ጥይት ከድንጋይ ተፈናጥራ እግሬን መታችኝ። አሁን እግሬ ከጉልበቴ አካባቢ ተሰብሯል”

“መሽቶ ነበረ። ወደ ሳዑዲ ድንበር እየተጓዝን ነበር። የሳዑዲን የድንበር ጠባቂዎች አየናቸው። እንድንቆም አዘዙን። ከዛም ወደኛ እየቀረቡ መጡ። እየተራመዱ ይተኩሱብን ጀመር። አንድ ጥይት ከድንጋይ ተፈናጥራ እግሬን መታችኝ። አሁን እግሬ ከጉልበቴ አካባቢ ተሰብሯል”

ሌላው በዚህ ሪፖርት ላይ ቃሉን የሰጠ ፍልሰተኛ ያጋጠማቸውን ክስተትና በደል እንዲህ ገልጿል።

“ተኩሱ ሲያቆም የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች ወሰዱን። የተያዝነው ሰባት ነበርን። 5 ወንዶች እና ሁለት ሴቶች። ድንበር ጠባቂዎቹ ልብሳችንን አስወልቀው “ሴቶቹን ድፈሯቸው” አሉን። ልጃገረዶቹ የ15 ዓመት ልጆች ነበሩ። ከመሃከላችን አንደኛው እምቢ አለ። ድንበር ጠባቂዎቹ እዛው ገደሉት። ልጆቹን ተገድደን እንድንደፍር የተደረግንበት ላይ እኔም ተሳትፌያለሁ። አዎ ህይወቴን ለማትረፍ ስል አደረኩት። ልጃገረዶቹም እምቢ ስላላሉ ህይወታቸው ተርፏል። ይህ ሁሉ የተፈፀመው እዛው የግድያው ቦታ ላይ ነው።”

የመብት ተቋሙ 42 ኢትዮጵያዊያንን ያናገረ ሲሆን 38ቱ ፍልሰተኞችና 4 ደግሞ ቤተሰብና ወዳጆች መሆናቸውን ገልጿል። 350 ቪድዮዎችን፣ ፎቶግራፎችን፣ በማኅበራዊ መገናኛዎች የተጋሩ መረጃዎችንና የመቶዎች ኪሎ ሜትሮች ርዝመት ያለውን የሳዑዲ-የመን ድንበር የሳተላይት ፎቶግራፎችን መመርመሩንና ለሪፖርቱ ግብዓትነት መጠቀሙን አስታውቋል።

የሳዑዲ የድንበር ጠባቂዎች ከሚይዟቸው ተሽከርካሪዎች በአንዱ ላይ ከባድ የጦር መሳሪያ የመሰለ ነገር በሳተላይት ካነሳቸው ምስሎች ማግኘቱን ገልጾ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ግለሰቦችም ይህንን እንዳረጋገጡለት አመልክቷል።

ተራራው ላይ ለአምስት ቀናት ያህል ተጓዝን። በቡድን ሆነን ነበር የምንጓዘው። በትንሹ 300 እንሆናለን። አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። ከዛ ከድንበር ጠባቂዎቹ ተተኮሰብን። ግዙፍ ሮኬት ነበር የተኮሱብን። ከ300ው 150ዎቹ ሞቱ”

“ተራራው ላይ ለአምስት ቀናት ያህል ተጓዝን። በቡድን ሆነን ነበር የምንጓዘው። በትንሹ 300 እንሆናለን። አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። ከዛ ከድንበር ጠባቂዎቹ ተተኮሰብን። ግዙፍ ሮኬት ነበር የተኮሱብን። ከ300ው 150ዎቹ ሞቱ”

ፍልሰተኞቹ በህገወጥ የሰው አሸጋጋሪዎች ሰሜናዊ የመንን በተቆጣጠሩት በሁጢ ታጣቂዎች በመታገዝ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሻገር ይሞክራሉ።

አሸጋጋሪዎቹ አልታበት እና አልራቅዋ የሚባሉ ሁለት ማቆያ ካምፖችን ያዘጋጁ ሲሆን ወደዚያ ለመግባትም ሆነ ከካምፑ ለመውጣት የሁጢዎቹን ፍቃድ ማግኘት እንደሚያስፈልግ መግለፃቸው ሰፍሯል።

ምንም እንኳ እስካሁን የተገደሉት ቁጥር በእርግጠኝነት ባይታወቅም አልራቅዋ ካምፕ አካባቢ ስምንት የወል መቃብሮች መኖራቸውን ህዩማን ራይትስ ዋች ያረጋገጠ ሲሆን ሪፖርቱ በተጠናቀረበት ከመጋቢት 2014 ዓ.ም. እስካለፈው ሰኔ 2015 ዓ.ም. በነበረው ጊዜ ውስጥ 287 መቃብሮችን ከሳተላይት ምስሎች ላይ ማግኘቱን ገልጿል። ይሁን እንጂ በየቦታው የተጣሉና አፈር ያልለበሱ አስከሬኖች በመኖራቸው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከሚገመተው የበዛ ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል።

ሪፖርቱ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችና ከለላ ጠያቂዎች ደርሶባቸዋል ያለውን ጥቃቶችና በደሎች ዝርዝር ያሠፈረ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምርመራ እንዲያደርግ ጠይቋል።

የሳዑዲ መንግሥት ይህንን ፖሊሲውን ባስቸኳይ እንዲያቆምና በግልፅ ተጠያቂ እንዲሆን ህዩማን ራይትስ ዋች አሳስቦ የመንግሥታቱ ድርጅትና የሚመለከታቸው ሃገሮች ጫና እንዲያደርጉ ጥሪውን አስፍሯል።

በግምት 750 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እንዲሚኖሩና እንደሚሠሩ፣ ብዙዎቹ ከሃገራቸው የወጡት ድኅነትንና የበረቱ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችን እየሸሹ መሆኑን ቡድኑ አመልክቷል። የቅርቡ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትም ለብዙዎች ስደት ሰበብ መሆኑን ጠቁሟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG