የሳዑዲ አረቢያ የወሰን ዘቦች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችንና ከለላ ጠያቂዎችን መግደላቸውን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ቡድን ህዩማን ራይትስ ዋች ዛሬ አስታውቋል።
ድንበር ጠባቂዎቹ በኢትዮጵያዊያኑ ላይ የመንና ሳዑዲ አረቢያ ድንበር ላይ ግድያውን የፈፀሙት ከመጋቢት 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ባስታወቀበት ሪፖርቱ አድራጎቱ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ቡድኑ ጠቁሟል።
እንዲህ ዓይነቱ በፍልሰተኞች ላይ ግድያ መፈፀም የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ፖሊሲ ከሆነ “በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል” ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች ጠርቶት የመንግሥታቱ ድርጅት ምርመራ እንዲያደርግ አሳስቧል።