በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሞኑ የደቡብ አፍሪካ ሁኔታ እና ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪካ


የደቡብ አፍሪካ ፀጥታ አስከባሪ ጉዳት በደረሰባቸውና በተዘረፉ አካባቢዎች እየተዘዋወረ ሲሆን ጁብላኒ የተባለው የገበያ ቦታ ከወደመና ዘረፋ ከተፈፀመበት በኋላ። ሐምሌ 6/2013
የደቡብ አፍሪካ ፀጥታ አስከባሪ ጉዳት በደረሰባቸውና በተዘረፉ አካባቢዎች እየተዘዋወረ ሲሆን ጁብላኒ የተባለው የገበያ ቦታ ከወደመና ዘረፋ ከተፈፀመበት በኋላ። ሐምሌ 6/2013

ቀውሱ በይበልጥ ካጠቃቸው ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው የደርባን ከተማ ናት። በከተማዎ ውስጥ ወደ 19 ዓመታትን ለሚጠጋ ጊዜ የኖሩት አቶ ያሬድ ክብረት እንደተናገሩት በከተማዋ የደረሰ ጥፋት በእጅጉ የከፋ ነው።በጆሃንስበርግ እና በፕሪቶሪያ የሚገኙ ሁለት የማኅበረሰብ መሪዎችም በተመሳሳይ የደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው እስካሁ ሕይወቱ ያለፈ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በደቡብ አፍሪካው ብጥብጥ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 212 ደርሷል። በግድያው፣ ዘረፋና ብጥብጡ የተጠረጠሩ 2500 ሰዎች ታስረዋል። የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማን እስር ተከትሎ በሃገሪቱ ለአንድ ሳምንት የቆየውን አመፅና ብጥብጥ እንደሚያስቆሙ እና ሁኔታዎች ወደነበሩበት እንዲመለሱ እንደሚያደርጉ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፖሳ ቃል ገብተዋል።

አያይዘውም ቀውሱ እና ብጥብጡ የታቀደ እና የተቀናጀ በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች በሕግ ይጠየቃሉ ብለዋል። በአሁኑ ሰዓት ብጥብጡን እንዲያቆሙ የተላኩት 25 ሺሕ ወታደሮች ኩዋዙሉ ናታል እና ጋተንግ በተባሉ አካባቢዎች የተንሠራፋውን ብጥብ እና ዘረፋ ያስቆማል ብለዋል። ሃገሪቱ አመፁ የተቀሰቀሰው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በሙስና ወንጀል የተከሰሱበት የፍርድ ቤት ጉዳይ ጥፋተኛ በመባላቸው እና ፍርድ ቤቱ የፈረደባቸውን የ15 ወራት እስር እንዲፈፅሙ ከታሰሩ በኋላ ነው።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የሰሞኑ የደቡብ አፍሪካ ሁኔታ እና ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:18 0:00


XS
SM
MD
LG