ዋሽንግተን ዲሲ —
በቂልንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ታሳሪ ቤተሰቦቻቸውን አግኝተው ምግብ ማቀበል እንዳልቻሉና ሲያገኟቸውም ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ችግር ስላለባቸው ችግራቸው እስኪፈታ ምግብ እንደማይቀበሏቸው እንደነገሯቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ልጅ ወ/ት ቦንቱ በቀለና የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ ባለቤት ወ/ሮ አሰለፈች ሙላት ዛሬ ወስደውት የነበረውን ስንቅ ይዘውት ወደቤት እንደተመለሱ ሲናገሩ የሕግ ጠበቃቸው ደግሞ ደንበኞቻቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ