በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዐቢይ አሕመድና ዊሊያም ሩቶ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን አጠናከሩ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ በናይሮቢ፤ ኬንያ፤ እአአ የካቲት 28/2024
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ በናይሮቢ፤ ኬንያ፤ እአአ የካቲት 28/2024

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ እና የኬኒያን የምጣኔ ሐብት ደረጃ ለማሳደግ ይችሉ ዘንድ ሁለቱ ሀገሮች ላይ የተጋረጡ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚፈልጉ ተናገሩ።

ኬኒያ ጉብኝት ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ረቡዕ ባደረጉት ንግግር "በክልላችን ብዙ ችግሮች አሉብን ፣በኢትዮጵያም በኬኒያ ብዙ ችግሮች አሉ። ተጨማሪ ችግሮች አንፈልግም። የኛ ፍላጎት የሁለቱን ሀገሮች ኢኮኖሚ ደረጃን ከፍ በማድረግ የጋራ ችግሮችን እየፈታን ሀገሮቻችንን ለተቀሩት አፍሪካዊያን ወንድሞቻችን አርአያ ማድረግ ነው”ብለዋል፡፡

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባደረጉላቸው የምሳ ግብዣ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለው የሀገሮቻቸውየሁለትዮሽ ግንኙነት "አፍሪካን በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም ነፃ ለማውጣት አርአያ ሆኖ ቆይቷል” ብለዋል።

ፕሬዚደንት ሩቶ በበኩላቸው ኬኒያ እና ኢትዮጲያ “ከፊታቸው ያሉትን ግዙፍ የሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም የምጣኔ ሐብት ዕድገት ዕድሎች በወንድማማችነት እና በስትራተጂያዊ ትብብር መንፈስ ሥራ ላይ ለማዋል በይበልጥ ተቀራርበው ለመሥራት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ዕርግጠኞች ነን” ብለው “ሁለቱ ሐገሮች አጋርነታቸውን ለቀጣናችንም ሆነ በአጠቃላይ ለአፍሪካ የዕድገት ቀንዲል እና የመልካም ሥራ ተምሳሌት ለማድረግ ሊሠሩ ዝግጁ መሆናቸውን እንተማመናለን” ብለዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎቹ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር የባህር በርን ለማግኘት በያዘችው ድርድር ዙሪያም መወያየታቸውን የአሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባው አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር እኤአ ጥር 1 ቀን የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመች ሲሆን ሶማሌላንድን እንደ ግዛቷ የምትቆጥረው ሶማሊያ የሰነዱ መፈረም አስቆጥቷታል፡፡ ለጦርነት ዝግጁ መሆኗንም አስታውቃለች። ሶማሌላንድ በበኩሏ “ኢትዮጵያ በባሕር በሩ አጸፋ እንደ ነጻ ሀገር እውቅና ልትሰጠን ተስማምተናል” ብላለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG