በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኬኒያ ጉብኝት ላይ ናቸው


 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ በናይሮቢ፤ ኬንያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ በናይሮቢ፤ ኬንያ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋ ጉብኝት ኬኒያ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩን የኬኒያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አሶሽየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ከተገነጠለችው ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋራ የባሕር በር ለማግኘት በተፈራረመችው መግባቢያ ሰነድ ጉዳይ እንደሚነጋገሩ ተጠብቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌስቡክ ገጻቸው ባወጡት ጽሑፍ "ፕሬዚደንት ሩቶን ስላደረጉልን ደማቅ አቀባበል አመሰግናለሁ” ያሉ ሲሆን "በዛሬው ውይይት ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን ያካተተ ውይይት አድርገናል” ብለዋል።

አያይዘውም “ውይይታችን የቆየውን ትስስራችንን ያጠናከረ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ቁልፍ የትብብር መስኮችንም የለየ ነበር” ያሉት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር የጋራ ራዕይ እና ዕጣ ፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመሥራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል” ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው አስነብበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG