በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የሰው መፈናቀልና ሞት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል"- የፓርላማ አባል


በዛሬው ዕለት ውይይቱ ለሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ የፓርላማ አባላቱ
በዛሬው ዕለት ውይይቱ ለሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ የፓርላማ አባላቱ

99 በመቶ በኢሕዴግ አባላት የሚመራው የኢትዮጵያው ፓርላማ አባላት ሰዎች ከቀያቸው እየተፈናቀሉና እየሞቱ ውይይት ሊደረግ አይገባም ሲሉ ለዛሬ ተጠርቶ የነበረውን የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም በተመለከተ የተዘጋጀን የዐዋጅ ረቂቅ ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ አራዘሙት።

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም በተመለከተ የተዘጋጀን የዐዋጅ ረቂቅ አስመልክቶ ውይይት ለማድረግ በሕግና ፍትሕ ጉዳዮችና በከተማ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተጠርቶ የነበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ አባላቱ “በሀገሪቱ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ እያለ በዚህ ላይ አንወያይም” በማለታቸው ውይይቱ ተቋርጦ ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን የፓርላማው አባላት ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።

በተጨማሪውም የዐዋጁ ረቂቅ በሕዝብ ውይይት ሳይደረግበት ሊፀድቅ አይገባም ተብሏል። ከቋሚ ኮሚቶዎቹ ሰብሳቢ አንዱ ጥያቄው ተገቢ በመሆኑ ውይይቱ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

"የሰው መፈናቀልና ሞት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል"- የፓርላማ አባል
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:33 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG