በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን


ፋይል ፎቶ - ሩዶልፍ ግራዝያኒ ንግግር እየሰጠ
ፋይል ፎቶ - ሩዶልፍ ግራዝያኒ ንግግር እየሰጠ

ዕለቱን አገር ውስጥ ያሉ ብቻ ሳይሆኑ ከአገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በተለያየ ዝግጅቶችና ፕሮግራሞች ያስታውሳሉ።

የፋሽሽት ኢጣልያ ጦር ኢትዮጵያን በ1928 ዓ.ም. በወረረ ባመቱ፣ ጨካኙ ሩዶልፍ ግራዝያኒ አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ አካሄደ።
በዚያ ቀን፣ ልክ የዛሬ 79 ዓመት፣ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በተካሄደው ጭፍጨፋ አዲስ አበባና አካባቢዋ ውስጥ ብቻ ወደ 30 ሺህ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። ዕለቱም "የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን" ተብሎ እነሆ እስከ ዛሬ ይታወሳል።
የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀን፣ ዘንድሮ 79ኛ ዓመቱ ላይ ነው። ዕለቱን አገር ውስጥ ያሉ ብቻ ሳይሆኑ ከአገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በተለያየ ዝግጅቶችና ፕሮግራሞች ያስታውሳሉ። Global Alliance For Justice in Ethiopia-ማለትም የኢትዮጵያ ጉዳይ የመፍትሔ አፈላላጊ ቡድን የሆነውና "ፍትህ ለኢትዮጵያ" የተሰኘው ስብስብ፣ የዘንድሮውን የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን በክብር ለማሰብ በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ከፕሮግራሙ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑትን አቶ ከባዱ በላቸውን፣ አዲሱ አበበ በ "ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ" ዝግጅቱ እንግዳ አድርጓቸዋል።
"የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን"
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:59 0:00

XS
SM
MD
LG