በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከመፈታት በኋላስ?


የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺና በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ሥር ከታሰሩ ከዘጠኝ ወራት በኋላ በ50 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር ተለቀዋል። ጽዮን ግርማ የእስር ቤት ቆይታቸውና ከእስር በኋላ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል ጠይቃቸዋለች።

በመጀመሪያ የአያያዝ ሁኔታቸው ዳንኤል ሺበሺ ድብደባ እንደደረሰበት በዚህም ምክንያት የጆሮው ታምቡር መጎዳቱን እና ይህም በሕክምና መረጋገጡን ተናግሯል። በቂልንጦ ቆይታቸው ደግሞ እጅግ የተጨናነቀ መቆያ እንደነበራቸው ተናግረዋል። ከእስር ከወጡም በኋላ ሁኔታዎች የባሱና ተስፋ አስቆራጭ ሆነው እንዳገኟቸው ገልፀውልናል።

ከጽዮን ግርማ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ከመፈታት በኋላስ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG