በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እስረኞችን ጎበኝቷል


ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች በአዲስ አበባ የታሰሩ የፖለቲካ እሰረኞችንና ጋዜጠኞችን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር በሚገኝ የታሳሪዎች ማቆያ ቦታ ድረስ በመሄድ የጎበኝዋቸውና በርካታዎቹንም ያነጋገሯቸው መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እነ አቶ ጅዋር መሃመድ፣ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ታሳሪዎች በቁጥጥር ስር በዋሉበት ጊዜም ሆነ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከመጡ በኋላ ስለደረሰባቸው የአያያዝ ችግር ያነጋገሯቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በሌላም በኩል ሰሞኑን ከፍተኛ ችግር ተከስቶባቸዋል የሚባሉትን እንደ ሻሸሜን፣ ምዕራብ አርሲ እንደ አርሰ ነገሌ፣ ኮፈሌ አካባቢ ተፈጸመዋል የተባሉትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተከታተሉ መሆኑንም አውስተው፣ በጠቅላላው በቅርቡ የደረሰውን ጉዳት መጠንና የሰብአዊ መብት ጥሰት ዓይነት “ለይተን ለመዘገብ፣ ለወደፊትም መደረግ የሚገባውን ምክረ ሀሳብ ለማቅረብ፣ አጥፊ የሆኑትን ወገኖችንም ተጠያቂነት ለማረጋገጥና ምርመራ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ” እንገኛለን ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እስረኞችን ጎበኝቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:41 0:00


XS
SM
MD
LG