ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ ውስጥ ዘር ተኮር ግጭቶች ሁሉንም ወገን የሚያሳስቡ ናቸው። በተለይ በቅርቡ ቡራዩ ውስጥ የተከሰተው ግጭት፣ ለሰው ሕይወትና ንብረት መጥፋት ምክንያት ከመሆኑ ባሻገር፣ ቀድሞ ተቻችሎና ተፈቃቅሮ የኖሩ ማህበረሰቦችን እያራራቀ ይመስላል።
ሕይወታቸው ለጠፋና ንብረቶቻቸው ለወደሙባቸው ወገኖችም፡ ፍትሕና ጥቃት አድራሾቹም በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ እየተጠየቀ ነው።
በሃገሪቱ ሰላም ለማስፈንና የተጀመረውን የፖለቲካ ለውጥ ለማስቀጠል፡ መገናኛ ብዙሃንና ማህበረሰብ ሚዲያዎች ሃላፊነት አለባቸው። በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ለውጡ እንዲመጣ ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉ ወጣቶች ለዘላቂነቱ ምን ሚና ይኖራቸዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ