በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምሥራቅ ኦርቶዶክ ክርስትና አማንያን የልደት በዐል


የኢትዮጵያ የተዋህዶ ሃይማኖት ካህን መንበሩን ሲያጥኑ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ እአአ ሚያዝያ 11, 2015 [ፋይል ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS]
የኢትዮጵያ የተዋህዶ ሃይማኖት ካህን መንበሩን ሲያጥኑ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ እአአ ሚያዝያ 11, 2015 [ፋይል ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS]

የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዐል ዋዜማ ዛሬ ታኅሣሥ 27 ቀን 2008 ዓም በመላው ዓለም በሚገኙ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ይከበራል። በኢትዮጵያም በዓሉ ዛሬ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በሚካሄድ ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ሲከበር ቆይቶ፣ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ የቅዳሴው ሥርዓት ይካድና ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጠቅላላ በዓሉ ይጠናቀቃል።

የልደት በዓል ብዙውን ጊዜ ታኅሣሥ 29 ቀን ነው የሚውለው። በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ግን፣ ያም፣ ጱሜን 6 በምትሆንበት ዓመት፣ በዐሉ እንዲህ እንደ ዘንድሮው ታህሣሥ 28 ቀን ይከበራል።

ይሁንና፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ-ልደቱ ታኅሣሥ 29 በመሆኑ፣ በዘመነ ዮሐንስ የሚመጣውን የ28 ቀንን በዓል የማይቀበሉ፣ ይልቁንም የተለመደውንና የጥንቱን ታኅሣሥ 29ን የሚያከብሩ፣ በዚሁ በታኅሣሥ 29 ቀን "ዮም ተወልደ" "ጌታ ዛሬ ተወለደ" ብለው የሚዘምሩ ሊቃውንት ጥቂት አይደሉም። እንደ ምሳሌም የላስታን፣ የጎንደርንና የአክሱምን ሊቃውንት ያስታውሷል።

ለምንድነው ይህን ጉዳይ ቤተ-ክኣህነቱ እልባት የማያደርግለት? ምንም እንኳ ቅዱስ ሲኖዶስ የልደት በዐል በዘመነ ዮሓንስ ታኅሣሥ 28 እንዲከበር ቢወስንም፣ ይህ የቀን ቀመር ስህተት አለበት የሚሉ ሊቃውንት ብዙ ናቸውና፣ መቼ ነው መስተካከልና ሊቃውንቱም መስማማት የሚችሉት?

የአዲስ አበበኣ ልዩ ዘጋቢያችን ንጉሤ አክሊሉ ሊቃውንትን ጠቅሶ በዚህ ዙሪያ ያቀናበረውን ዘገባ፣ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የምሥራቅ ኦርቶዶክ ክርስትና አማንያን የልደት በዐል
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:58 0:00

XS
SM
MD
LG