መቀሌ —
ከ60 በላይ የትግራይ ክልል ራማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ትናንት መረብ ተሻግረው የኤርትራ ከተማ በሆነችው ክሳድ ዒቃ ከኤርትራውያን ጋር ውለው ተመልሰዋል።
አዲስ ዓመት 2011 በመረብ ወንዝ አብረው ለማሳለፍ ቀጠሮ መያዛቸው ለቪኦኤ ተናግረዋል።
በጉዟቸው የኤርትራ ወታደሮችም በድንበር አካባቢ የተቀበረ ፈንጅ እንዳይኖር ፈትሾ በሰላማዊ መንገድ እንዲገቡ እንዳገዛቸው ገልፀዋል።
ከ60 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከራማ ከተማ እሰከ የኤርትራዋ ከተማ ክሳድ ዒቃ ሞተር ብስክሌት ነው የተጓዙት።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ