የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የባንክ ሒሳቡ እንዳያንቀሳቅስ በኤርትራ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን በመታገዱ የአስመራ በረራውን ማቋረጡን አስታወቀ፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሠው በሰጡት መግለጫ፣ የኤርትራ ሲቪል አቭዬሽን ባለሥልጣን ቀደም ብሎ ስላስተላለፈው የበረራ እገዳ ውሳኔም ሆነ ቀጥሎ በመጣው የባንክ ሒሳብ እግድ ጉዳይ ዙሪያ ለመወያየትም ሆነ ለማብራራት ፈቃደኛ አልሆነም ብለዋል፡፡ በዚህ የተነሳም አየር መንገዱ ‘ከዛሬ ጀምሮ የአስመራ በረራውን አቋርጧል’ ብለዋል።
መድረክ / ፎረም