በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ አስመራ አልበርም አለ


ፋይል፡ የኢትዮጵያ ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላን በማረፍ ላይ
ፋይል፡ የኢትዮጵያ ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላን በማረፍ ላይ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ የሚያቆም መሆኑን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ኤክስ በተሰኘው የማሕበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ከነገ ነሃሴ 28, 2016 ዓም ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ የሚያቋርጥ መሆኑን ለደንበኞቹ መግለጽ ይወዳል፤ ብሏል።

አየር መንገዱ ወደዚያ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለማቋረጥ ለወሰደው ውሳኔ ኤርትራ ውስጥ ያጋጠመው ‘እጅግ አዳጋች’ ያለውን የሥራ ሁኔታ በምክኒያትነት ጠቅሷል። ይሁን እንጂ ጽሁፉ አየር መንገዱን ‘ገጠሙት’ ያላቸውን ሁኔታዎች ምንነት አያብራራም።

በአውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ከመስከረም 30 አንስቶ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያቋርጥ የኤርትራ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን በጻፈው ደብዳቤ መጠየቁን አየር መንገዱ ባለፈው ሃምሌ ወር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

የበረራ መቋረጡ ከተባለው ቀን ቀደም ብሎ መጀመሩ በምን ምክንያት እንደሆነ አየር መንገዱ ግልፅ አላደረገም።

የኤርትራው የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድን “በተደራጀ እና ስልታዊ በሆነ ዘዴ የመንገደኞችን ሻንጣ በመስረቅ፣ ጉዳት በማድረስ፣ በማዘግየት እና ሲጠፋም ካሳ ባለመክፈል” ወንጅሎ፣ ወደ አሥመራ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያቋርጥ አስታውቆ ነበር።

ባለሥልጣኑ አቀርብኩት ያለውን ቅሬታ እንዲያስተካከል አየር መንገዱን ቢጠይቅም፣ ለችግሩ መፍትሄ ሊገኝ እንዳልቻለም አስታውቋል።

በኤርትራ ባለስልጣናት የቀረቡትን ወንጀላዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ውድቅ አድርገዋል።

መንገደኞች የሻንጣ ስርቆት ድርጊት እንዳልገጠማቸው የገለፁት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ለሻንጣ መዘግየትም አየር መንገዱ መፍትሄ እንደሰጠ አክለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG