በትናንትናው ዕለት የአዲሱን የአውሮፓዊያን ዓመት ዘገባውን ያወጣው የመብት ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ወች እ.ኤ.አ. የ2016 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የጭካኔና ገደቦች ዓመት ብሎታል። ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባወጀችበት በዚህ ወቅት መሰረታዊ መብቶችን በመገደብና ሰለማዊ ሰልፈኞች ላይ የከፈተችዉን ደም አፍሳሽ አፈናን ቀጥላበታለች ብሏል። በኤርትራም የዜጎች ሰብአዊ መብቶችን መጣሷን ቀጥላበታለች ብሏል። የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ መንግሥት የሂዩማን ራይትስ ወችንም ሆነ የሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችን ሪፖርቶች እንደማይቀበሉ በተለያየ ጊዜ ሲናገሩ ይደመጣል።
የአሁኑን የ2017 የሂዩማን ራይትስ ወች ሪፖርት በተመለከት የኢትዮጵያው ሪፖርት ላይ ምላሻቸን እንዲሰጡን ለኢትዮጵያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጽ/ቤት እና የኤርትራውን ሪፖርት በተመለከት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ጋርደውለን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ጽዮን ግርማ በሂውማን ራይትስ ወች ከፍተኛ የአፍሪካ ተመራማሪ የሆኑት ፌሊክስ ሆርን ስለሪፖርቱ አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።
ዝርዝርሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።