በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ ፖሊዮ ከታየ ሰላሣ ሦስት ወራት አለፉ


ፎቶ - ፋይል
ፎቶ - ፋይል

ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ሰላሣ ሦስት ወራት የፖሊዮ አጋጣሚ አለማታየቱን አንድ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሙያ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ዛሬ በዓለም ዙሪያ ታስቦ የዋለውን የዓለም ፀረ-የልጅነት ልምሻ ቀን አስመልክቶ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከዓለም ሃገሮች ዘጠና ዘጠኝ ከመቶው ከፖሊዮ ነፃ ሲሆኑ ከዓለም ሕዝብ ሰማንያ ከመቶ የሚሆነው የሚኖረው ከፖሊዮ ነፃ በሆኑ አካባቢዎች እንደሆነ ታውቋል፡፡

ፖሊዮን የማጥፋት ዘመቻ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከተጀመረበት ከ1981 ዓ.ም ወዲህ ባለፉት ሃያ ስምንት ዓመታት ውስጥ በተደረጉ ጥረቶች ሊጠፋ የተቃረበው ፖሊዮ ካገረሸ በዓመት እስከ 200 ሺህ የሚደርሱ ሕፃናት በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ በልጅነት ልምሻ እንደሚጠቁ የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት ዋና ዳይሬክተር ቶም ፍሪደን ተናግረዋል፡፡

በያዝነው የአውሮፓ 2016 ዓ.ም ፓኪስታንና አፍጋኒስታን ውስጥ ሰባ አራት አዳዲስ የልጅነት ልምሻ አጋጣሚዎች መታየታቸውን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

አንዲት ሃገር ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ፖሊዮ ካልታየባት የፖሊዮ ነፃ እንደሆነች እንደሚቆጠር ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ድንበር ዘለል የሆነውን ይህንን የሕፃናት ጤናና የአካል ጉዳት ችግር ለመከላከል ከሁሉም ጎረቤት ሃገሮች ጋር እየሠራ መሆኑን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶችና ሕፃናት ጤና ክፍል የክትባት መርኃግብር ኃላፊው አቶ ጌትነት ባየ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ፖሊዮ ከታየ ሰላሣ ሦስት ወራት አለፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:31 0:00

XS
SM
MD
LG